የአማራ ክልል ምክር ቤት አቶ አረጋ ከበደን በፕሬዚደንትነት ሰየመ

"የአማራን ሕዝብ ትግል ውስብስብ ነው፤ ወጥ ዓላማ፣ የጋራ ራዕይ፣ በቂ የትግል ስልትና የሌሎችን አሰላለፍ ያልተረዳ በመሆኑ ፈታኝ አድርጎታል" - ተሰናባች የአማራ ክልል ፕሬዚደንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

Arega Kebede.png

Arega Kebede, newly appointed President of Amhara Regional State. Credit: AMC

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዓርብ ነሐሴ 19 የአክልሉን የሰላምና ደህንነት ሁኔታ አስመልክቶ በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የርዕሰ መስተዳድር ለ23 ወራት የቆዩበትን መንግሥታዊ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ በምትካቸው አቶ አረጋ ከበደ ተተክተዋል።

ምክር ቤቱ ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ ለክልሉን የፀጥታ ሁኔታ ዕልባት ለማበጀት በነደፈው የለውጥ የድርጊት መርሃ ግብር ዕቅድ ላይ ከስምምነት ላይ መድረሱም ተገልጧል።

ዶ/ር ከፋለ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር "የአማራን ሕዝብ ትግል ውስብስብ ነው፤ ወጥ ዓላማ፣ የጋራ ራዕይ፣ በቂ የትግል ስልትና የሌሎችን አሰላለፍ ያልተረዳ በመሆኑ ፈታኝ አድርጎታል" በማለት አንኳር ያሏቸውን ችግሮች አመላክተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ የቀድሞውን ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ የአቶ አረጋ ከበደን ርእሰ መስተዳድርነት ሹመት ያጸደቀው ምክር ቤቱ በአዲሱ ርዕሰ መስተዳድር በእጩነት የቀረቡትን የተለያዩ ሹመቶች ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

በዚሁ መሠረት፤

1.አቶ አብዱ ሁሴን የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

2. ዶ/ር አሕመዲን መሐመድ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ

3. ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ

4. ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

5. አቶ ደሳለኝ ጣሰው በምክትል ርዕሰ መስዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ

6. ዶ/ር ጋሻው አወቀ የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኃላፊ

7. አቶ ብርሃኑ ጎሽም የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ

8.ዶክተር መንገሻ ፈንታው የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

9. ዶ/ር ስቡህ ገበያው የአማራ ክልል ሥራ እና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ

10. አቶ ክብረት አህመድ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

11. አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ

12. ዶ/ር ደመቀ ቦሩ የአማራ ክልል ፕላን እና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

 ከላይ የተጠቀሱት ተሿሚዎች በእጩነት የቀረቡ ሲሆን ሌሎቹ ተቋማት ባሉበት እንደሚቀጥሉ ርዕሰ መስተዳድሩ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የምክር ቤት አባላቱ በዕጩ ተሿሚዎች ላይ ሰፊ ውይይት እና ምክክር ካደረጉ በኋላ ሹመታቸውን አጽድቀዋል፡፡

 





Share

Published

Updated

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
የአማራ ክልል ምክር ቤት አቶ አረጋ ከበደን በፕሬዚደንትነት ሰየመ | SBS Amharic