የፊፋ የዓለም ዋንጫ 2022ᵀᴹ በቀጥታና በነፃ እንደምን በ SBS ራዲዮ መስማት እንደሚችሉ

ከኳታር በቀጥታ በመላው አውስትራሊያ የሚሰራጨውን እያንዳንዱን የፊፋ የዓለም ዋንጫ 2022™ በ SBS ራዲዮ ያድምጡ።

Cameroon's goalkeeper Gael Ondoua (L) and Brazil's Neymar (R) on office buildings in Doha, Qatar.jpg

Cameroon's goalkeeper Gael Ondoua (L) and Brazil's Neymar (R) on office buildings in Doha, Qatar. Credit: EPA / NOUSHAD THEKKAYIL/EPA/AAP Image

የፊፋ የዓለም ዋንጫ 2022™ ኖቬምበር 21 ቀን 2022 / ኅዳር 12 ቀን 2015 ይጀምራል። በመላ አውስትራሊያ የ SBS ቀጥታ ስርጭትም በነፃ ይተላለፋል። 64ቱም ግጥሚያዎች በሙሉ፤

  • DAB ዲጂታል ራዲዮ
  • ኦንላይን sbs.com.au/radio
  • በSBS ራዲዮ iOS እና Android ሞባይል ኧፕ ያድምጡ።

    እንደምን መስማት እንደሚችሉ
ለፊፋ የዓለም ዋንጫ 2022™ ስርጭት በተመደቡ ጣቢያዎቻችን SBS Football 1, 2 እና 3 በ DAB ራድዮንዎ፣ በድረገጽ SBS Radio website ወይም በ SBS ነፃ ራዲዮ ኧፕ እያንዳንዱ ግጥሚያ በ12 ቋንቋዎች በቀጥታ ይሰራጫል።

  • SBS Football 1 (ስርጭቱን ጀምሯል)፤ በእያንዳንዱ ግጥሚያ ወቅት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማብራሪያዎች፣የዓለም ዋንጫ ዋነኛ ሙዚቃንና ሌሎችንም ወቅቶች ያክላል።
  • SBS Football 2 and 3 (ኖቬምበር 14 / ኅዳር 5 ይጀምራል)፤ የእያንዳንዱን የተጋጣሚ ቡድናት ጨዋታዎች በቀጥታ በተለያዩ ቋንቋዎች ያሰራጫል።
  • SBS Arabic24፤ እያንዳንዱን ግጥሚያ በአረብኛ ቋንቋ ያስተላልፋል።

    ከመላው ዓለም በፊፋ የዓለም ዋንጫ™ አማካይነት ከሽርካዎች የሚቀርቡ ማብራሪያዎች በ SBS በኩል በአረብኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፖርቹጋል፣ፈረንሳይኛ፣ ጀርመን፣ ዳች፣ ክሮኤሽያ፣ ፖሊሽ፣ ጃፓንኛ፣ ኮሪያ፣ ፐርዥያና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ይቀርባሉ።


    ውድድሮቹ በሚካሔዱበት ወቅት SBS ራዲዮ 3 ወደ SBS እግር ኳስ 2 በመለወጥ እያንዳንዱን ግጥሚያ በተለያዩ ቋንቋዎች ያሰራጫል። በውድድሮቹ ጊዜያት የ BBC World Service ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭትን ለማድመጥ BBC Sounds website ይጎብኙ።

    የእግር ኳስ ትኩሳት መዝሙሮች

    ከቀጥታ የእግር ኳስ ስርጭት ውጪ ካለፉት የዋንጫ ውድድሮች አንስቶ ጥሩና መጥፎ የተሰኙ የብሔራዊ ቡድኖች ሙዚቃዎችን አካትቶ ያለማቋረጥ የሚተላለፉት የእግር ኳስ ገናና ሙዚቃዎች ይቀርቡበታል። የዓለም ዋንጫ ተሞክሮዎን ቀደም ብለው አሁኑኑ የ SBS Football 1 እና DAB ራዲዮ ወይም በ SBS Radio website በማድመጥ ይጀምሩ።
  • የፊፋ ዓለም ዋንጫ 2022ᵀᴹ ቀናትና ሰዓታት

    የSBS ራዲዮ የተለያዩ ቋንቋ ማብራሪያዎች ሠንጠረዥ የውድድሩ መጀመሪያ ሲቃረብ ማስተካከያ የሚደረግበት ይሆናል።

    • የቡድን ደረጃ: ኖቬምበር 21 - ዲሴምበር 3 / ኅዳር 12 - 24
    • የ16 ቡድናት የዙር ግጥሚያ: ዲሴምበር 4 - 7 / ከኅዳር 25 - 27
    • ሩብ ፍፃሜ: ዲሴምበር 10 - 11 / ከታህሳስ 1 - 2
    • የመጨረሻ ማጣሪያዎች: ዲሴምበር 14 - 15 / ከታህሳስ 5 - 6
    • የ3ኛ እና 4ኛ የደረጃ ግጥሚያ: ዲሴምበር 18 / ታህሳስ 9
    • የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ: ዲሴምበር 19 / ታህሳስ 10
    ቋንቋ ስርጭት ሽርካዎች፤ BBC, Radio Nacional de España, Radio France Internationale, BAND, beIN, RTP, ARD, SRF, RNE, Radio Oriental Montevideo, HRT, RFI, NHK, NOS, VRT, Polskie Radio, Seoul Broadcasting Systemን ያካተተ ነው።

    .


Share

Published

By Kassahun Seboqa Negewo, SBS Radio
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service