አውስትራሊያ ውስጥ በድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ወይም ከመግቢያው ስድስት ሜትሮች ርቀት ላይ የምርጫ ቅስቀሳን የሚያግድ የቆየ ድንጋጌ አለ።
የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን መራጮች በድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶችን የሚያንፀባርቁ ካናቴራዎችን ከመልበስና ደረት ላይ ተለጣፊ ምልክቶችን ሰክቶ ከመገኘት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
በታካይነትም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ቶም ሮጀርስ መራጮች እርስ በእርሳቸው መልካም ሥነ ምግባርን በተላበሰ ሁኔታ እንዲተያዩ ጠይቀዋል።
ከወዲሁ ከቅዳሜው የሕዝበ ምርጫ ቀን ቀደም ብለው አራት ሚሊየን መራጮች ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማን አስመልክተው ተጨማሪ መረጃ ካሹ SBS አማርኛን ይከታተሉ። በተለይ በነባር ዜጎች ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረውን የ SBS NITV ይመልከቱ፤ እንዲሁም SBS Voice Referendum portal እና Voice Referendum hub on SBS On Demand ድረ ገፆችን ይጎብኙ።