ለድቁና ታስቦ ለሙዚቃ መድረክ የበቃው ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ"

Elias Yemane Kiwi.jpg

Singer Elias "Kiwi" Yemane. Credit: E.Yemane

ድምፃዊ ኤልያስ የማነብርሃን ዳምጤ በቅፅል መጠሪያ ስሙ "ኪዊ" ተብሎ ይጠራል። ኒውዚላንድ በአንድ ወቅት ጥላ ከለላው ነበረችና የአገረ ኒውዚላንድ መለያ ቅፅል ስምን ይጋራል። ኤልያስ ለመድረክ የበቃው ድምፁን በሙሉቀን መለሰ ዘፈኖች አሟሽቶ፤ በጥላሁን ገሠሠ ቅላፄ ቃኝቶ ነው።


ኤልያስ፤ የሕይወት እስትፋንስን ለመጀመሪያ ጊዜ የማገውና በቤተሰቦቹ ዕቅፍ ውስጥ የገባው ወላጆቹ ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ ለሽርሽር ሔደው ሳለ ነው።

እስካሁንም የሕይወቱ አካል ሆኖ ያለው የሙዚቃ ዓለም ግና የተገኘው የአባቱ የሊቀ ጠበብት የማነብርሃን ዳምጤ የደም ሐረግ ውርስ ነው፤ ምንም እንኳ ከድምፃዊነቱ ይልቅ ድርሰት፣ ትወና፣ ሥነ ስዕልና ዳንስ ቀዳሚ የሙያ ዝንባሌዎቹ ቢሆኑም።

ወደ ሙዚቃ ተስቦ በድምፃዊነት ለመድረክ እንዲበቃ የገደምዳሜ ተፅዕኖ ያሳደሩበት ግና የዘመናዊ ሙዚቃ አፍቃሪና የታላቁ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ወዳጅ የነበሩት አጎቱ ናቸው።

ኤልያስ በሙሉቀን መለሰ ድምፁን አሟሽቶ፤ በጥላሁን ገሠሠ ቃኝቶ የ1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት ለወለዳቸውና አያሌ ዝነኛ አንጋፋ ድምፃውያንን ላፈሩት የቀበሌና ከፍተኛ መድረኮች አቀንቃኝነት በቃ።

ከከፍተኛ ወደ ግራር የምሽት ክለብ ገባ። ሲልም፤ ሒልተን፣ አሮሠና ስቴሪዮ ክለቦች ታከሉ።

ለድቁና ታስቦ ዓለማዊ የሙዚቃ መድረክ ላይ ያረፈው ድምፃዊ ኤልያስ የሥነ ጥበብ ብርቱ ማለፊያ ተፅዕኖ ሲገልጥ፤
ሥነ ጥበብ ግንዛቤን ይፈጥራል፤ ሰዎች የመንፈስና ባሕላዊ ዝግጅት እንዲኖራቸው ያደርጋል። አገራዊ የማንነት ዕሴቶቻችን አስተሳስሮ ያነቃል።
በሚል ነው።

በሶማሊያ አቋርጦ፣ በኒውዚላንድ ጠለላ፣ አውስትራሊያን ሁለተኛ አገሩ አድርጎ በስደት የተለያት ውድ አገሩ ኢትዮጵያን ከአድማስ ባሻገር በማማተር።

በቀጣዩ ክፍል ለስደት ወጥቶ በሞቃዲሾ ስታዲየም ዝናን እንደምን እንዳተረፈ ያወጋል።

Share
Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ለድቁና ታስቦ ለሙዚቃ መድረክ የበቃው ድምፃዊ ኤልያስ "ኪዊ" | SBS Amharic