Settlement Guide: What is elder abuse? How to recognise and prevent it

በቤተሰብ መካከል መለያየት ሲፈጠር በአብዛኛው የአረጋውያን ለጉስቁልና መዳረግ ሁነት ይጨምራል። እንዲህ ያለው ነገር በእርስዎ ላይ ከደረሰ ወይም በሌሎች ላይ ደርሶ ካዩ ለመግታት የሚያስችል እርምጃ መውሰድ በጣሙን ጠቃሚ ነው።

Elder abuse

Elder abuse Source: AAP

ወደ አውስትራሊያ መጤ ለሆኑ አረጋውያን ማኅበራዊ ገለልተኝነትና የቋንቋ ችግር፣ ለጉስቁልና በሚዳረጉበት ወቅት አቤቱታ ለማቅረብ እንዳይችሉ ተጨማሪ መሰናክሎች ይሆኑባቸዋል። ይሁንና መጤ ማኅበረሰባትን ለመርዳት የሚያስችሉ እገዛዎች አሉ።

አረጋውያንን ለጉስቁልና መዳረግ ምንድነው?

የዓለም የጤና ድርጀት አረጋውያንን በአንድ ወቅት ወይም በተደጋጋሚ ሆን ብሎ ማጎሳቆል፣ ወይም "በእምነት ማጉደል ሳቢያ ለጉዳት ሲዳረጉ፣ አለያም አንድ አረጋዊ ግለሰብ ለጭንቀት ሲጋለጥ" ተገቢ እርምጃን አለመወሰድ አረጋውያንን ለጉስቁልና እንደመዳረግ ይፈርጀዋል።
24783292-7bf2-4dd1-ab79-1fe1dd5858c2_1496885063.jpeg?itok=c56d4Aor&mtime=1496885106


አረጋውያንን ማጎሳቆል ከዓለም ሕዝብ 10 ፐርሰንቱን ቢያካትትም ብዙውን ጊዜ ግና በሪፖርትነት አይቀርብም።

90 ፐርሰንት ያህሉ አረጋውያንን ለጉስቁልና የመዳረግ ሁነቶች ተከስተው ያሉት በቤተሰብ አባላት ነው። የAdvocare ዋና ሥራ አስፈጻሚ ግሬግ ማህኒ “የAdvocare ተሞክሮዎችና ጥናታዊ ምርምሮች የሚያሳዩት በአብዛኛው አረጋውያንን ለጉስቁልና ዳራጊዎች ሴቶችና ወንዶች ልጆች መሆናቸውን ነው የሚያመለክቱት” ብለዋል። 

World Health Organisation

NSW Seniors Rights Service

Seniors Rights Victoria
ውስን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ወይም የትምህርት ደረጃ ያላቸው አረጋውያን በአብዛኛው በቤተሰባቸው ወይም በጓደኞቻቸው ለመጎሳቆል የተጋለጡ ናቸው።

ምልክቶቹ ምንድናቸው?

7f2be959-7c30-47e7-9f36-33e5b109ff9c_1496884999.jpeg?itok=-Xu6K5WN&mtime=1496885023


ውስን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ወይም የትምህርት ደረጃ ያላቸው አረጋውያን በአብዛኛው በቤተሰባቸው ወይም በጓደኞቻቸው ለመጎሳቆል የተጋለጡ ናቸው።

አንዳንዴ በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጉስቁልናዎችን በውል ለመለየት ያውካል። የተካሄደባቸው የጉስቁልና ተግባር ምናልባትም የረቀቀ ይሆናል፤ አሊያም አረጋውያኑ ስለ ጉዳዩ መናገር አይሹም። ለምሳሌ ያህል፣ ከአንድና ሁለት የቤተሰብ አባላት ባሻገር የማኅበረሰብ ድጋፍ የሌላቸውን አረጋውያን ለመጠቀሚያነት የሚገለገሉባቸውም ሰዎች አሉ። 

 “እንዲህ ላሉ ሰዎች አረጋውያን ስለምን እንደሚፈርሙ በማያውቁት ጉዳይ ላይ እንዲፈርሙ ማስደረግ በጣሙን ቀላል ነው።” የአረጋውያን መጦሪያ፤ ሥራ አስኪያጅ አሌግዛንደር አብራሞፍ 

Aged Rights Advocacy Service 

አንዱ የተዘወተረ አረጋውያን ጉስቁልናን የማድረሻ መንገድ ንዋይ ነው

አረጋውያንን ለጉስቁልና መዳረግ በአካል ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ ሥነ ልቦናዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ማግለልንም ያካትታል።

ይበልጡኑ ተዘውትሮ የሚከሰተው ግና ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ነው። ከአረጋውያን ገንዘብን በመስረቅ፣ የውርስ ሰነዶችን እንዲለውጡ ማስገደድ ወይም የባንክ ዶክሜንት ላይ ፊርማቸውን አስመስሎ መፈረምን ያካትታል።
8669884b-444a-4a41-9dc6-ed70becf387c_1496884860.jpeg?itok=MVoeYmDB&mtime=1496884874


የተወሰኑ ሰዎች የነገረ ፈጅ ሥልጣንን በመጠቀም የገንዘብና ሕጋዊ ጉዳዮቻቸውን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር አረጋውያንን ለጉስቁልና ይዳርጋሉ። 

“የቋንቋ ችሎታ ውስንነት የመጤዎችን ብይነመረብ ያጠብባል፤ እንዲሁም በፋይናንስና ሕጋዊ ውሳኔዎቻቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል።” - የአረጋውያን መጦሪያ፤ ሥራ አስኪያጅ አሌግዛንደር አብራሞፍ

The Australian Institute of Family Studies

NSW Seniors Rights Service

እገዛን እንደምን ያገኛሉ?

f94f1677-650e-4d9c-9937-e5ea792d0683_1496884903.jpeg?itok=8xLUMeuC&mtime=1496884913


 

በየትኛውም የአውስትራሊያ ክፍለ ሃገራትና ክፍለ ግዛታት ውስጥ በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጉስቁልናዎች አስመልክቶ ሪፖርት ማድረግን ግድ የሚያሰኙ ድንጋጌዎች የሉም።

ይሁንና፤ እያንዳንዳቸው ክፍለ ሃገራትና ክፍለ ግዛታት ለጉስቁልና የተዳረጉ አረጋውያንን የሚያግዝ ተቋማት አላቸው። በራስዎ ላይ ደርሶ ከሆነና እንዲሁም ሌላ ለጉስቁልና የተዳረጉ አረጋውያንን የሚያውቁ ከሆነ ሁሌም ለችግሮቹ አሥፈላጊውን እርዳታ የሚቸሩ አሉ።

My Aged Care website በመጎብኘት በሚኖሩበት ክልል እርዳታ ሰጪ ተቋማትን ይፈልጉ።   
ራስዎ ወይም ሌሎች አረጋውያን ለጉስቁልና ከተዳረጉ አሥፈላጊውን እርዳታን የሚሰጥ አለ።
ሆኖም ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች እንግሊዝኛ ቋንቋን በውል የማይናገሩ ከሆነ ችግርን ሪፖርት ማድርግ አዋኪ ይሆናል። ከእንግሊዝኛ ሌላ ቋንቋን የሚናገሩ ከሆነ ብሔራዊ የትርጉምና ትርጁማን አገልግሎትን (TIS) በ 13 14 50 ደውለው ያነጋግሩ። ራስዎ ደውለው መነጋገር የማይችሉ ከሆነ ግና ሐኪምዎን፣ የሃይማኖት መሪዎን ወይም እምነት የሚጥሉበትን ወዳጅዎን ደውለው እንዲያነጋግሩልዎት ማድረግ ይችላሉ።

Australian Institute of Family Studies

The National Translating and Interpreting Service (TIS) 

ግንዛቤን ማስጨበጥ

57193703-b56c-4abb-b22a-39668ffea521_1496884939.jpeg?itok=DBht1tSE&mtime=1496884954


 

የተባበሩት መንግሥታት ራስን መቻል፣ ተሳትፎ፣ ክብካቤ፣ ራስን ለስኬት ማብቃትንና ለአረጋውያን ክብር የማጎናጸፍን መርሆዎች ይደግፋል።

በአብዛኛው አረጋውያን በራሳቸው ቤተሰብ አባላት ለጉስቁልና እንዳይዳረጉ ጁን 15 ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ጉስቁልና ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን እንዲሆን ይሁንታን የቸረው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ነው። 

የዚህ ዓመት ግንዛቤ ማስጨበጫ ቃል ‘የአረጋውያን ጉስቁልናን ማስቆም እንችላለን’ የሚል ነው። በማኅበረሰብ ዝግጅት ወይም በራስዎ ዝግጅቶችን በማስተናገድ መሳተፍ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል፣ በዕለቱ ሐምራዊ ልብስ በመልበስ፣ ዛፍ በመትከል፣ የጠዋት ሻይ በማዘጋጀት፣ አለያም የእግር ጉዞ በማሰናዳት ግንዛቤን ማስጨበጥ ይችላሉ።

በይበልጥ ለመረዳት፤ 

UN Principles for Older Persons (1991)

Elder Abuse Awareness day

በቋንቋዎ መረጃን ያፈላልጉ:

በ Elder Abuse Helpline

ጠቃሚ ሊንኮችና ስልክ ቁጥሮች

Victoria: Seniors Rights
Helpline: 1300 368 821

NSW: Police - Elder Abuse
Helpline: 1800 628 221

Western Australia: Advocare
Helpline: 1300 724 679 (Perth)

1800 655 566 (rural)

ACT: Elder Abuse prevention and assistance

Helpline: 02 6205 3535

Northern Territory: Emergency Services
Helpline: 131 444

Queensland: Elder Abuse Prevention Unit
Helpline: 1300 651 192

South Australia: Aged Rights
Helpline: 08 8232 5377 (Adelaide)

1800 700 600 (rural)

Tasmania: Advocacy Tasmania
Helpline: 1800 441 169


Share
4 min read

Published

Updated

By Ildikó Dauda
Presented by Kassahun Seboqa

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service